ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Tuesday, 27 July 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

በመምሬ የአድባር ዛፍ ሲል ምን ማለት ነው? ብታስረዱኝ

ኦሪት ዘፍጥረት
13፥18
አብራምም ድንኳኑን ነቀለ መጥቶም በኬብሮን ባለው በመምሬ የአድባር ዛፍ ተቀመጠ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ።
14፥13
አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊ መምሬ የአድባር ዛፍ ይኖር ነበር እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።
14፥23-24
አንተ፦ አብራምን ባለጠጋ አደረግሁት እንዳትል፥ ብላቴኖቹ ከበሉት በቀር ከእኔ ጋር ከሄዱትም ድርሻ በቀር፥ ፈትልም ቢሆን የጫማ ማዘቢያም ቢሆን፥ ለአንተ ከሆነው ሁሉ እንዳልወስድ አውናን ኤስኮልም መምሬም እነርሱ ድርሻቸውን ይውሰዱ።
18፥1
በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት።
23፥17
በመምሬ ፊት ያለው ባለድርብ ክፍል የሆነው የኤፍሮን እርሻ ለአብርሃም ጸና
23፥19
ከዚህም በኋላ ኬብሮን በምትባል በመምሬ ፊት በከነዓን ምድር ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ አብርሃም ሚስቱን ሣራን ቀበረ።
25፥9
ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤልም በመምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬጢያዊ በሰዓር ልጅ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።
35፥27
ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ አብርሃምና ይስሐቅ እንግዶች ሆነው ወደ ተቀመጡባት ወደ መምሬ ወደ ቂርያትአርባቅ እርስዋም ኬብሮን ወደምትባለው መጣ።
49፥30
እርስዋም በከነዓን ምድር በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊ ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት፥ ባለ ድርብ ክፍል ዋሻ ናት።
50፥13
ልጆቹም ወደ ከነዓን ምድር አጓዙት፥ ባለ ሁለት ክፍል በሆነች ዋሻም ቀበሩት እርስዋም በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊ ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት ዋሻ ናት።
Jul 23, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

1 መልስ

+1 ድምጽ
መምሬ (Mamre) የሰው ስም ሲሆን፤ የአንድ አሞራዊ ሰው ስም ነው። ይህ ሰው ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን ያደረገ ሰው ነው።
Quote:
ኦሪት ዘፍጥረት
14፥13 አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊ መምሬ የአድባር ዛፍ ይኖር ነበር እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር

በዚህ በአሞራዊው መምሬ (Mamre) መሬት ላይ አንድ ትልቅ ዛፍ ነበር። ይህ ዛፍ የእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ የoak ዛፍ እንደሆነ ይገልጻል፤ አማርኛው ደግሞ የአድባር ዛፍ ይለዋል። በአማርኛው አድባር ይለዋል ሆኖም የዛፉን አይነት መለያ ማለትም ልክ የግራር ዛፍ ወይም የባህር ዛፍ ወዘተ እንደሚባለው የዛፉን አይነት የሚጠቅስና ትልቅ ዛፍ እንደሆነ ለማሳየት ነው እንጂ፤ በተለምዶ "አድባር" ተብሎ የባህል አምልኮ የሚደረግበት ለማለት አይደለም። ስለ አድባር ዛፍ ወይም በእንግሊዝኛው oak ዛፍ የበለጠ ለመረዳት እዚህ ተጭኖ ማንበብ ይቻላል።

አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲያውም በተሻለ ሁኔታ "ትልልቅ የመምሬ ዛፎች" በማለት ይተረጉመዋል። ምክንያቱም "አድባር" ተብሎ በቀድሞው ትርጉም የተተረጎመው የዛፉን ወይም የዛፎቹን ትልቅነት ለማሳየት እንጂ ባህላዊ አምልኮን ለማመልከት አይደለምና። ደግሞ አማርኛው እንጂ "አድባር" የሚለው በእብራይስጡም ይሁን በእንግሊዝኛው እንዲህ ያለ ባህላዊ አምልኮን የሚያመለክት ምንም ነገር ስላለተጻፈ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተሻለ ሁኔታ ተርጉሞታል።

በዘፍጥረት ላይ እንግዲህ በመምሬ የአድባር ዛፍ ሲል የሚናገረው በአሞራዊው መምሬ (Mamre) መሬት ላይ ስላለ አንድ ትልቅ የOak ዛፍ ነው። ማለትም አንዳንዴም ኬብሮን ተብሎ የሚጠራውን ቦታ ለመጥቀስ ነው፤ እንጂ በአማርኛው ብቻ አንብበነው ስለ አንድ አድባር ባህላዊ አምልኮ የሚደረግበት ዛፍ ነው ብለን እንዳንወስደው መጠንቀቅ ያስፈልጋል። እነዚህ ክፍሎች አንዳቸውም ስለ ባህላዊ የአድባር አምልኮ የሚናገረ ወይም የሚያመለክት ነገር የላቸውም። የዛፍ አይነት ለመጥቀስ እንጂ።
Jul 25, 2011 በቃሉ (2,230 ነጥቦች) የተመለሰ
ጌታ ይባርክህ ተመልሶልኛል
"አድባር" የሚለው ቃል ከየት እንደመጣ ለማወቅ ፈልጌ በቂ ማብራሪያ አጥቻችለሁ። እዚህ ከላይ የተጠቀሰው ጽሁፍ የ "አድባር" ቃል አቀማመጡ በቅድመ ጣኦታዊ አምልኮት ግዜ የነበረ ትርጉሙን ይዞ የመስላል። የጣኦታዊ ትርጉም ሰጪ ቢሆን በዚያን ግዜ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ አይገባም ነበር። ስለዚህ የቃሉ ትርጉም እኛ አሁን ከምናውቀው የተለየ ትርጉም አለው ማለት ነው።

በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች "አድባር" የሚለው እንደ እንስት የሆነች ምድርን፣ ከባቢውን፣ ቀበሌውን ሀላዊ(ጠባቂ)ፍጥረት ስም ተደርጎ ይወሳል። በአንዳንድ የቀያይ አሜሪካዊ ጎሳዎሽ ውስጥ የዚች እንስት መኖር ተዓማኒነት አለው። ማለት ከላይ የጠቀስኩት ገለጻ በአሜሪካውያን በሁር ተወላጆችም እንደ እምነት ተይዞ ያለ ጉዳይ ነው ማለት ነው። በኢትዮጵያውም በአሜሪካኖቹም እምነት ይቺ እንስት ያካባቢው አረንጓዴ ሲመነጠር ይከፋታል፣ ሰደድ እሳት የተንሳ እንድሆን፣ ዛፎች የተጨፈጨፉ እንድሆን፣ የዱር እንሥሣት ለጨዋታ እየታደኑ የተጨረሱ እንደሆነ ይከፋታል፣ መካፋቷ ለከት ካለፈ እልቂት ታመጣለች ተብሎ ይታመናል። በኢትዮጵያ እንደማውቀው መለማመኛ ድርጎት የሰጣል፣ ፈንዱሻ ይበተናል፣ የመስዋእት ፍሪዳ ይታረዳል።

ይህንን ሁሉ የጻፍኩት "አድባር" የሚለው ቃል "the environment" የሚለውን ቃል ይተካል ወይ ለማለት ነው። በዚህ ይዘቱ ከሆነ ግን "አድባር" የሚለው ቃል እንዲያውም ከበድ እና ጠለቅ ያለ ትርጉም ያለው ስለሆነ ኢትዮጵያውያን አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ እና እንዲከባከቡ ጥሩ የስያሜ ማጎልበቻ ይሆናል ማለት ነው።
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...