መምሬ
(Mamre) የሰው ስም ሲሆን፤ የአንድ አሞራዊ ሰው ስም ነው። ይህ ሰው ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን ያደረገ ሰው ነው።
Quote:
ኦሪት ዘፍጥረት
14፥13 አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊ መምሬ የአድባር ዛፍ ይኖር ነበር እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።
በዚህ በአሞራዊው መምሬ
(Mamre) መሬት ላይ አንድ ትልቅ ዛፍ ነበር። ይህ ዛፍ የእንግሊዝኛው መጽሐፍ ቅዱስ የ
oak ዛፍ እንደሆነ ይገልጻል፤ አማርኛው ደግሞ የአድባር ዛፍ ይለዋል። በአማርኛው አድባር ይለዋል ሆኖም የዛፉን አይነት መለያ ማለትም ልክ የግራር ዛፍ ወይም የባህር ዛፍ ወዘተ እንደሚባለው የዛፉን አይነት የሚጠቅስና ትልቅ ዛፍ እንደሆነ ለማሳየት ነው እንጂ፤ በተለምዶ "አድባር" ተብሎ የባህል አምልኮ የሚደረግበት ለማለት አይደለም። ስለ አድባር ዛፍ ወይም በእንግሊዝኛው
oak ዛፍ የበለጠ ለመረዳት
እዚህ ተጭኖ ማንበብ ይቻላል።
አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲያውም በተሻለ ሁኔታ "ትልልቅ የመምሬ ዛፎች" በማለት ይተረጉመዋል። ምክንያቱም "አድባር" ተብሎ በቀድሞው ትርጉም የተተረጎመው የዛፉን ወይም የዛፎቹን ትልቅነት ለማሳየት እንጂ ባህላዊ አምልኮን ለማመልከት አይደለምና። ደግሞ አማርኛው እንጂ "አድባር" የሚለው በእብራይስጡም ይሁን በእንግሊዝኛው እንዲህ ያለ ባህላዊ አምልኮን የሚያመለክት ምንም ነገር ስላለተጻፈ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተሻለ ሁኔታ ተርጉሞታል።
በዘፍጥረት ላይ እንግዲህ በመምሬ የአድባር ዛፍ ሲል የሚናገረው በአሞራዊው መምሬ
(Mamre) መሬት ላይ ስላለ አንድ ትልቅ የ
Oak ዛፍ ነው። ማለትም አንዳንዴም ኬብሮን ተብሎ የሚጠራውን ቦታ ለመጥቀስ ነው፤ እንጂ በአማርኛው ብቻ አንብበነው ስለ አንድ አድባር ባህላዊ አምልኮ የሚደረግበት ዛፍ ነው ብለን እንዳንወስደው መጠንቀቅ ያስፈልጋል። እነዚህ ክፍሎች አንዳቸውም ስለ ባህላዊ የአድባር አምልኮ የሚናገረ ወይም የሚያመለክት ነገር የላቸውም። የዛፍ አይነት ለመጥቀስ እንጂ።