ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Sunday, 29 November 2020
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

ለወደፊቱ ኑሮዬ ዋስትና አጣሁ

በጌታ ፍቅር ሰላም እላችሁዋለሁ!
እኔና ባለቤቴ ከተጋባን ስምንት አመት ሆኖናል፡፡ ነገር ግን ከጋብቻችን ጥቂት ወራቶች ጀምሮ ሁለት እህቶቹ በትዳራችን ጣልቃ እየገቡ ብዙ ሰላም የሚነሱኝን ድርጊቶች ሲፈጽሙ ባለቤቴ ነገሩን እንደቀላል እያየ በማለፉ ለእኔ ትዳሬ የልቅሶ ሆኖብኝ ስምንቱን አመታት በሃዘን አሳልፌያቸዋለሁ፡፡ በየምክንያቱና እሱ የሌለበትን ወቅት እየጠበቁ ለሱ የማልመጥን መሆኔን ሊያሳውቁኝ ይሞክራሉ፡፡ ጥቅም ነክ ነገር ሲፈልጉ እርሱን ለብቻ ይጠይቃሉ፡፡ ጉዳዩን ግን ከእርሱው እሰማዋለሁ፡፡ ከቤት እነርሱ ካሉና እንዳጋጣሚ የኔ ቤተሰቦች ከመጡ የንቀት ድርጊቶችን ያሳያሉ፡፡ ባለቤቴ ግን ለእነርሱ ያለው ፍቅር የተለየ በመሆኑ እንባዬን እያየም ቢሆን እኔን ከመቆጣትና እነርሱንም አልፎ አልፎ ከመገሰጽ በቀር ችግሩን ምንነት አጥብቆ ለመጠየቅና መፍትሄውንም ለማምጣት አይፈልግም፡፡ እባክህን ችግራቸውን ጠይቅልኝ እኔም በድያቸው ከሆነ ጥፋቴን ይንገሩኝ እታረማለሁ ብለውም ቆይ እሺ ከማለት አላለፈም፡፡
በቤታችንም ከባለቤቴ ጋር የግል ጊዜ የሚኖረን መኝታ ላይ ብቻ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በየተራም ሆነ አብረው እየመጡ በእንግድነት ከቤት አይጠፉም፡፡ ስለዚህ እኔ እነሱን በማስተናገድና ልጆቼን ከማጫወት ያለፈ ተሳትፎ የለኝም፡፡
ብዙውን ጊዜ ፍቺ ብጠይቅስ እረፍት አገኛለሁ ብዬ አስብና የእግዚአብሔርን ነገር በማሰብ እሱው መፍትሄ ያምጣልኝ ብዬ እተወዋለሁ፡፡ የወለድናቸውም ልጆች ሰላም እንዳያጡ እሰጋለሁ፡፡
አሁን በቅርቡ ግን ለማንም ግልጽ በሆነ መልኩ ሊያለያዩን ከባድ ተንኮል ሸርበው ባለቤቴን በኔ ላይ እንዲነሳ አደረጉት፡፡ ነገሩን ሆኖአል ብሎ በማመኑ ባለቤቴ ክፉ ቃላትን በመናገርና እኔን በመወንጀል ንዴትና ጥላቻውን ሊያሳየኝ ተነሳ፡፡ እንደልማዴ እያለቀስኩ አለመፈጸሜን ባስረዳውም አላመነኝም፡፡ እነሱ ያሉትን ድርጊቶች ፈጸምኩ በተባለበት ወቅት የነበርኩበትን ሁኔታ እንዲያስታውስ ስናገረው ነገሮቹን በራሱ መንገድ አጣርቶ የተባለው ፈጽሞ ውሸት መሆኑን እንደተረዳ ከይቅርታ ጋር ገለጸልኝ፡፡ አሁንም ለምን እንዲህ እንዳደረጉ ቀርበው ይናገሩ ብለውም እነርሱ አልፈለጉም ብሎ ነገሩን ዘጋ፡፡ ከነርሱም ጋር በዚሁ ተለያየን፡፡
አሁን የምጠይቃችሁ ነገር ቢኖር ባለቤቴ የነርሱ ነገር እንደበቃውና እስከዛሬም ባለማወቅ እንደበደለኝ ይናገራል፡፡ ይህም ሆኖ ግን የሚናገረውና የማያቸው ሁኔታዎቹ የተለያዩ ሆነው ይሰማኛል፡፡ እየዞሩ ስሜን ያጠፉ እንደሆን አላውቅም አንዳንድ ዘመዶቹም በእንግድነት ሲመጡ ጥሩ ያልሆነ ፊት እያየሁባቸው ተቸግሬያለሁ፡፡ በዚህ ላይ እነዚህ እህቶቹ እንደቀድሞው ከቤት ባይመጡም በብዙ ይደዋወላሉ፡፡ ወደፊትም ቢሆን ነገር የተረሳ ከመሰላቸው ዳግመኛ ያገኘሁት ሰላም ለማደፍረስ በሌላ መንገድ ሊመጡ ይችላሉ ስልም አስባለሁ፡፡ በዚህ የተነሳ ለወደፊቱ ኑሮዬ ዋስትና አጣሁ ምንስ ላድርግ?
Aug 4, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ
Aug 10, 2011 ታርሟል
የጌታ ሰላም ይብዛልሽ
እኔ እንደሚመስልኝ የትዳራችሁ መሪ ማን ነው? እግዚአብሄር ከሆነ አሁንም እሱም ሆነ አንች ነገራችሁን በጌታ ፊት አብራችሁ ብታቀርቡ ከስጋት ልትድኝ ትችያለሽ ሌላው አብራችሁ የምትጽልዩበት ጊዜ የላችሁም
ለምን ባለቤትሽ ፊት ምን አጠፋሁ ብለሽ ለመጠየቅ አትሞክሪም? ፊት ለፊት የበደልኩዋችሁ ምንድን ነው ብለሽ ችግሩን ለመጋፈጥ ብትሞክሪ መልካም ነው

5 መልሶች

0 ድምጾች
ሰላምሽ ይብዛ ውድ እህታችን
እስቲ ትንሽም ቢሆን ከጌታ ጋር ያለሽን ነገር ነገሪን።
ሁለታችሁም ከሁሉም በላይ እርስበርሳችሁ በጌታ ወንድም እና እህት መሆናችሁን አትዘንጉ ያ ከማንም የስጋ ዝምድና ይበልጣል። በጌታ የሆንን እኛ በዚህ በምድር ብቻ ሳይሆን በዛኛውም ለዘላለም አብረን ነን። ለምድር ኑሮ ብሎ የዘላለሙ አይገፋም አስተውሉ። ባለቤትሽ እና ያንች የመንፈሳዊ ህይወት እንዴት ነው?
ተባረኪ
Aug 5, 2011 YaelD (8,160 ነጥቦች) የተመለሰ
ሰላምሽ ይብዛ የኒ እህት አንቺ እና ባለቢትሽ የ ወንግላዊ ደሞዝ እንዲት እንኑር የሚለውን 7 ክፍሎች ስብከትን ተከታተሉት
ባለቤቴ በፊት በጌታ ያለው ነገር ጠንካራ ነበር፡፡ አሁን ግን እሁድ እሁድ በቤተክርስቲያን አምልኮ ከመካፈል የዘለለ ነገር አላይበትም፡፡ በስራ ቀናት የሚደረጉ ፕሮግራሞች ላይ የመሄድ ፍላጎቱ ደካማ በመሆኑ ብቻዬን እሄዳለሁ፡፡ የጋራ ጸሎትም እንደተመቸው እና ደስ ካለው እናደርጋለን፡፡ ብዙውን ጊዜ ግን ብቻዬን በጌታ ፊት እንበረከካለሁ፡፡
እርግጥ ነው የቤቴ ራስ ክርስቶስ መሆኑን አምናለሁ፡፡ ግን ባለቤቴ ያለበትን ደካማ ጎን እህቶቹ ጠንቅቀው ስለሚያውቁና እኔም እስከዛሬ ያሳለፍኩት የምሬት ህይወት ስለሚያንገፈግፈኝ ስጋት በልቤ ውስጥ ይመላለስብኛል፡፡ ሰይጣንንም በጋራ ለመቃወም እንዳልኩዋችሁ የቤት ውስጥ ህብረታችን ደካማ ነው፡፡


ጌታ ይባርካችሁ!
0 ድምጾች
የጌታ ጸጋ ይብዛልሽ፡
እውነቱን ለመናገር ስለራስሽ ትጽፍአለሽ ብዬ ነበር ያስብኩት ግን "ባልቤቴ በፊት..... " በለሽ ጀመርሽ(ማቲ 7፡4-5)፤ ሁላችንም እራሳችን ሳናይ ሌላውን ማይት ይክብዳል።
ከሁሉ በፊት አንቺ ከጌታ ጋር ያለሽን ነገር ተመልከች፤ ምኑ ጋ ነው ቀዳዳ የከፋትኩት በላሽ አስቢ እና ንሰሃ ጊቢ እና ቤትሽን እና ልጆችሽን በጌታ ቃል ኮትኩቺ። ማንም በትዳርሽ እና ቤትሽ እዳይስልጥን ጌታን ሹሚው በቀን በቀን ቤትሽን በመዝሙር እና ቃል ትምህርቶች በመክፈት እና በማዳመት መንፈስሽን እና የቤትሽን ሁኔታ ለጌታ ለሆነ ነገር አስገዚ ጌታን ስታስቀድሚ የአንችም ስሜት ለመንፈስ ቅዱስ ሲገዛ ሰላምሽ ከሰው እዳልኖነ ታያለሽ ያኔ ለባልሽ ያለሽ ነገር ይቅየራል እርሱ ወንድምሽ ለዘላለም ባልሽ ደግሞ በዚህ በምድር እና እራስሽን ከ እህቶቹ ጋር አታወዳድሪ ። ትዳርሽ ከጌታ የትሰጠ አገግሎት አድርገሽ እይውና በነገር ሁሉ ባልሽን አስድስችው ጌታን በዛታስድስቻልሽ እና የተከበር እና ይተወደደ ባል ባንቺ ጌታን ማይት ይቀለዋል እንኻን ጌታን ያወቀ ወንድም ጌታን የማያውቅ እንካን ያስትውላል አብዝሽ ጸልይ የባልሽ ልብ ወደጌታ እንዲ መለስ ከእሁድ ያልፈ ኑሮ እዲሆን። የቤትሽ እራስ ባልሽ ነው የባልሽ እራስ ደግሞ ጌታ ነው ያንች ቀድም ተከተሉን አዛብቶ መጽፈ የሚያሳየኝ ምን አልባት ከምታልፊባት የተነሳ እርሱን ከቦታው አንስተሽው እዳይሆን እፈራልሁ ከሆነ fix it fast. ጌታ አክብሪው እርሱም ያከብርሻል። የባልሽ (እህት፡ የጽሎት ደጋፊ፡ ፍቅረኛ፡ የልጆቹ እናት) አንቺ ነሽ እና እሱን በነገር ማሃል ከማስገባት ፋንታ ከነገር ጋርጂው ሳሺለት በድካሙ በርታት ሁኝው ። ለሁለታችሁም የኑሮ ዋስትና የሆነውን ጌታን ተመልከቱ እርሱ የ እምነታችን ጀማሪ እና ፈጻሚ ነው።
አይዞሽ ጌታ ካንቺ ጋር ነው በምንም ነገር ቤትሽን ጥልሽ አትሂጂ ወደ ጌታ ቅረቢ እርሱም የቅርባሻል። ከመቼውም የበለጠ ከባልሽ ጋር ያለ ህብረት ይጠንክር።
ጌታ ይባርክሽ።
Aug 5, 2011 YaelD (8,160 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
ይህን ለሚያነቡ ሁሉ የጌታ ሰላም ይሁን። አሜን!!!

"እኔና ባለቤቴ ከተጋባን ስምንት አመት ሆኖናል፡፡ ነገር ግን ከጋብቻችን ጥቂት ወራቶች ጀምሮ ሁለት እህቶቹ በትዳራችን ጣልቃ እየገቡ ብዙ ሰላም የሚነሱኝን ድርጊቶች ሲፈጽሙ ባለቤቴ ነገሩን እንደቀላል እያየ በማለፉ ለእኔ ትዳሬ የልቅሶ ሆኖብኝ ስምንቱን አመታት በሃዘን አሳልፌያቸዋለሁ፡፡ ብዙውን ጊዜ ፍቺ ብጠይቅስ እረፍት አገኛለሁ ብዬ አስብና የእግዚአብሔርን ነገር በማሰብ እሱው መፍትሄ ያምጣልኝ ብዬ እተወዋለሁ፡፡ የወለድናቸ ውም ልጆች ሰላም እንዳያጡ እሰጋለሁ፡፡ አሁን በቅርቡ ግን ለማንም ግልጽ በሆነ መልኩ ሊያለያዩን ከባድ ተንኮል ሸርበው ባለቤቴን በኔ ላይ እንዲነሳ አደረጉት፡፡" ክብርት ውድ እህታችን ከዚህ ካካፈልሽን ውስጥ ከጥቂቱ ተነስቼ ትንሽ ሃሳብ እንድሰጥ ፍቀጂልኝ።

እህቴ! በመጀመሪያ ከዚህ ፍችን አልወድም ከሚለው እግዚአብሔር ሁኔታሽን ብቻ ሳይሆን ውስጥሽን ከሚያውቅ ታላቅ ዘላለማዊ ሁልን የሚያይ ሁሉን የሚያሰማ ሁሉን የሚያውቅ አምላክ ጋር መጣበቅን ስለ መረጠሽ እኔን ይክፋኝ እንጂ አልፋታም ጌታዬን አላሳዝንም ልጆቻችንም አይከፋቸውም ብለሽ እንድትወስኚ የረዳሽ ጌታ መንፈስ ቅዱስ ይመስግን። በዚህ ውሳኔሽ ጌታ ደስ መሰኘቱን ይህን ያህል ነው ብሎ ለመገመት በጣም ከባድ ነው ግን በእምነትሽ እጅግ ደስ ስላሰኘሽው የጠላትንን ወሽመጥ ቆርጠሽዋልና በርቺ ጽኚ። ንጉስ ዳዊት መነሳቴን መቀመጤን ከሩቁ ታውቃለህ አለ። እባክሽን የኢዮብን ፈተና አስቢና ራስሽን አበርቺ ተስፋሽን እንዲያድስልሽ በብርቱ ጸልይ። እስከ መስቀል ሞት ድረስ ነውኮ የወደደን።

ባልሽ ካንቺ ጋር መነጋገር ለምን እንዳልፈለገ የጠላት ስራ ነውና አባቴ እባክህ እርዳን ልባችንን ጠብቅልን ብለሽ ለምኚው። ጌታ ካንቺ ጋር ነውና ተዋጊ በጌታ ከአሸናፊዎች በላይ ነን ይላል ቃሉ ስለዚህ ጽኚ በቅርቡ ባልሽ ወደ ልቡ ይመለሳል ምን ነክቶኝ ነው እንዲህ ያደረጉት እያለ በቅርቡ እባክሽ ይቅርታ አድርጊልኝ ብሎ ይጠይቅሻል አንቺ ግን ሙሉ ይቅርታ ለማድረግ ከአሁኑ ተዘጋጂ፡፡

እነዚያ በሰው ትዳር ውስጥ መግባትና ችግር መፍጠሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አለመሆኑ ያላስተዋሉት "እህቶች" ናቸው ለማለት ያዳግታል ግን ማን ነው የማይበድል ማን ነው የማይሳሳት ማን ነው ተንኮል የማያስብ የጌታ ምህረት ግን አያልቅምና ስንቴ ነው ምህረት ያገኘነው? ይኸው እሳካሁን ደርስ በህረቱ ቁመናል። የጠላት መጠቀሚያ የሆኑትን እነዚህ እቶችን አንቺ ነሽ ነጻ የምታወጫቸው ስለዚህ ሁሌ በጸሎት እያቀረብሽ ባርኪያቸው ክልብ ደግሞ እንድወዳቸው እርዳን ብለሽ ለሚኚ። ባለሽባት ቤተ ክርስቲያን ባለሽበት አካባቢ በብርቱ ጸሎት ከሰጠሽ ሰው ጋር ጸልዩና የእነዚህ እህቶች ነፍስን ለማትረፍ እንዲያነጋግሩዋቸው እንዲመክሩዋቸው እንዲመልስዋቸው አርምጃ ውሰጂ።

ጌታ መንፈስ ቅዱስ መሪነቱን ድጋፉን ያብዛላቹህ
ወንድምሽ
Aug 6, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Aug 6, 2011 ታርሟል
0 ድምጾች
የአንቺን ጥያቄ ሳነብብ ሁለት ነገር ነው የታየኝ።

አንደኛ ባልሽን የማጣት ፍርሃት። ሁለተኛ ከዚህም የተነሳ የራስሽ ትግልና ረፍት ማጣት።

ስለዚህ እኔ የምመክርሽ ባልሽን በፍቺ ብቻ ሳይሆን በሌላም ነገር ልታጭው እንደምትችዪ እንድታስቢ ነው። በሰው ላይ መታመምና መሞትም አለና። ስለዚህ የወደፊት ተስፋሽንና ሕይወትሽን በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ እንጂ በባልሽ ላይ አታድርጊ። አንቺ ስለ ፍቺ ስትጨነቂ፣ ነገ ባልሽ አንድ ነገር ቢሆንስ ምን ይውጥሻል? ስለዚህ አይንሽን ከባልሽ ላይ አንስተሽ በማይናወጠው ዓለት በአምላክሽ ላይ አድርጊ። ያለ ባልም ሊያኖርሽ በሚችል በአምላክሽ ታመኚ እንጂ፤ ልክ ያለ ባልሽ ሕይወት እንደሌለሽ አድርገሽ አትቁጠሪ።

በተቻለ መጠነም ልጆችሽ ካደጉና ያንቺን እርዳታ ካላስፈለጋቸው፤ ራስሽን ለማሻሻል ሞክሪ። ለምሳሌ ትምህርት በመማርና ሥራ በመሥራት፤ ከባልሽ ጋር ያለሽን ጥገኝነት ብትቀንሺ እጅግ መልካም ነው እላለሁ። ባልሽን ከማጣት ፍርሃት ነጻ ለመውጣት አንድ እገዛ ያደርግልሻላና።

በመጨረሻም የባልሽን ዘመዶች በፍቅር ለማሸነፍ ሞክሪ። ምንም ክፉ ቢያስቡብሽና ቢናገሩብሽም አንቺ ግን ፍቅርንና መልካምን ምግባር በማሳየት አሸንፊያቸው። ከሚጠበቅብሽ በላይ አንድ እርምጃ እየሄድሽ መልካምን በማድረግ፤ በተቸገሩ ጊዜ በመድረስ፤ ከሚጠበቅብሽም በላይ በማድረግ በፍቅር አሸንፊያቸው። ባልሽ የቤተሰቦቹን ክፋት አይቶ እነርሱን ይጠላል ወይም ከእነርሱ ይለያል ብለሽ የቂል ተስፋ አታድርጊ። ባልሽ ምንም ይሁን ምን ከቤተሰቦቹ ሊለይ አይችልም፤ በፍጹምም የማይሆን ነገር ነውና ራስሽን አታታልዪ። ይልቁኑ ባልሽን ለመለወጥ ሳይሆን፤ ዘመዶቹን በፍቅር ለማሸነፍ ሞክሪ።

ይህንን ሁሉ እያደረገሽና ሁል ጊዜም አይንሽን በአምላክሽ ላይ ካደረግሽ እከሌ ስለ እኔ ምን አለ፤ ስለ እኔ እነ እከሌ ምን አወሩ ወይም ምን ይሉ ይሆን እያልሽ ከመጨነቅ ትድኚያለሽ። የሚሉትን ይበሉ አንቺ ብቻ በአምላክሽ ፊት ቅን ሁኚ በእርሱም ታመኚ። የሚመጣውም ይምጣ፤ ምንም አትፍሪ። ክርስቶስን ማጣት እንጂ ባልን ማጣት የሕይወት መጨረሻ አይደለም። ይሄን ያህል በፍርሃት መኖር አያስፈልግም። ትልቁ የአንቺ ችግር ባልን ከማጣት የመነጨ ፍርሃት ይመስለኛልና፤ ይሄንን ፍርሃት ካሸነፍሽ መልካም የእረፍትና የእፎይታ ሕይወት የምትኖሪ ይመስለኛል።
Aug 8, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
+1 ድምጽ
በመጀመሪያ ደረጃ ምንም አታድርጊ፣ራስሽን አረጋግተሽ ቆም በይና አስቀድሞ ትዳርን ሳይሆን ሕይወትን የሰጠሽን ጌታ አስቢ፡፡ጌታ በዙፋኑ ላይ አለ፡፡

ለቀረብሺው ጥያቄ ምልሱን በሁለት አቅጣጫ እንመልከት፡፡
  • የሕይወታችንም ሆነ የምድር ኑሮአችን ዋሥትና፣ሳናውቀው ያወቀንና ወደ ፍቅሩ መንግሥት ያፈለሰን ፣በምድርም ሰላም ለእናንተ ይሁን ያለን፣ የሠላም አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡አስተማማኝ ዋስትናችን የማይናወጠው ዓለት ለተደገፉበት ሁሉ እውነተኛ መደገፊያ፣በየወቅቱ የሚነሱብንን ማዕበሎች ዝም አስኝቶ በሠላም የሚያሻግር፣አሁንም ለዘለዓለምም ያው የሆነው እርሱ በዙፋኑ ላይ ነው፡፡ስለዚህ በመጀመሪያ ደረጃ በትዳር ላይ ከመደገፍሽ በፊት በእርሱ ላይ መደገፍሽን ልብ በይ! እርሱ አይጥልሽም፣አይተውሽም፡፡ሠላም ይሁንልሽ፡፡
  • ሁለተኛው ከእናንተ ሁለታችሁ ከለጉዳዮቹ አንጻር፣ ( ተጋቢዎችን ማለቴ ነው፣)

ውድ እህቴ!

በአንቺ በጠያቂዋ በኩል ያየሁት በጣም ጥሩ ኳሊት(QUALITY ) አለ፡፡ ጠያቂነትሽ፣ምክር ፈላጊነሽ፣ለገጠመሽ ችግር መፍትሄ ፈላጊነትሽን በጣም በጣም አደንቃለሁ፡፡ትዳርሽን ከአደጋ ለማዳን እያደርግሽ ያለውን ጥረትም፣ ትዳር አክባሪነትሽንም ስለሚያመለክት ጥረትሽን አከብራለሁ፡፡

ተገቢውን አስተያየትም ሆነ የምክር ሃሳብ ለመሰጠት በመጀመሪያ የጀርባ ታሪካችሁን(Background) ማወቅ ይጥቅም ነበር፡፡

ሁለተኛ በአንቺ በኩል ያለውን ጉዳት ሰማን እንጂ እርሱን(ባለቤትሽን) አልሰማነውም፡፡ ዕድል አግኝተን ብንሰማው ኖሮ እርሱስ በበኩሉ ምን ይል ይሆን? ለምን እንባሽን እያየ በቁጣ ብቻ እንዳለፈ ከአፉ ብንሰማ ጠንከር ብለን ለማናገር ድፍረት ይኖረን ነበር፡፡ ለማንኛውም ጠቅለል ያለ ሃሳብ ለመስጠት በአጭሩ እንዲህ ማለት ይቻላል፡፡

እንደ መንፈሳውያን ሰዎች (ባለትዳሮች) መፈሳዊ ምክር ለመስጠት የሁለታችሁንም ትውውቅና የትዳሩ አጀማመር እንዴት እንደነበር ማወቅም ይጥቅመን ነበር፡፡ አመሠራረቱ ወይም የትዳሩ መሠረት ምን እንደሆነ ምክር ሰጪዎች ብቻ ሳይሆኑ ተመካሪዎቹም በውል ማወቅ ያለባቸው ይመስለኛል፡፡ለምን ከተባለ መሠረቱ የሁለቱም ተጋቢዎች ፈቃድና እውነተኛ መፈቃቀር ከሆነ ትዳሩን ደህንነት ለመጠበቅ የአንድ ወግን ጥረት ብቻ አይሆንምና ነው፡፡እንደዚህ ከሆነ (የአንዱ ብቻ መፍጨርጨር) በድካምና በተስፋ መቁረጥ እንዲሁም በሀዘን ከመማቀቅ ያለፈ ፋይዳ ያለው ነገር አይሆንም፡፡ ለምሳሌ፣ ጭብጨባ የምንወድ ከሆነ ሁለት እጆች ያስፈልጉናል፡፡ ግራ እጅ የቱንም ያህል ጭብጨባ ቢወድና ቢፈልግ ብቻውን አይችልም፡ሀርሞኒ(Harmony) ያለው ጭብጨባ ማምጣት ከፈለገ የግድ ቀኝ እጅ አብሮት ለማጨብጨብ እንዲነሳ ያስፈልገዋል፡፡ስለዚህ ግራ እጅ ቀኙን፣ ቀኙም እጅ ግራውን በመንከባከብና በመረዳዳት አብሮ ለማጨብጨብ በስምምነት መነሳሳት
አለባቸው፡፡በአጭሩ ትዳሩ እንዲያምርበትና በመልካም ትሥሥር ውጤታማ ቤተሰብ ለመምራት፣እንዲሁም የትዳሩን ጤንነትና ውበት ለማበላሸት ከሚሰነዘሩ ጎጂ ነገሮች መጠበቅና መጠንቀቅ የሁለታችሁም መሆን አለበት፣ካልሆነ የአንድ ወገን ብቻ ጥረት ውጤታማ አይሆንም ለማለት ነው፡፡

ቤተሰብ፣

ተፈላልጋችሁና ተዋዳችሁ የተጋባችሁት፣በሰውም በእግ/ርም ፊት ቃል ኪዳን የተሰጣጣችሁት(ከሆነ ? ) ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ፡፡ እሱም ሆነ አንቺ እንደ ክርስቲያኖች ከተጋባችሁ በየትኛውም መንገድ ኃላፊነቱን የወሰዳችሁ አሁንም ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ፡፡ኃላፊነቱን በውል ለመወጣትና ችግራችሁን በጋራ መፍታት ከፈለጋችሁና ጤናማ ትዳራችሁን ለመምራት ከፈለጋችሁ የሁለታችሁ ግልጽና ጠንካራ አቋም ያስፈልጋል፡፡ ቤተስብም ሆነ ሌላው ጣልቃ እንዲገባ ከፈቀዳችሁ ያላችሁ ዕድል እነርሱ የሚወስኑላችሁን የትዳር ዓይነት ተቀብላችሁ መኖር ብቻ ነው ፡፡ቤተሰብ በሩቅ ሆኖ ዕርዳታ ካስፈለገው ይረዳ፣ መርዳትም ከፈለገ ያለምንም ተጽዕኖ ነጻ ዕርዳታ ያድርግ፡፡በተረፈ የሁለቱን ሀርሞኒ የሞላበት ጭብጨባ ከሩቅ ቆሞ እየሰማ መደሰት ይችላል፡፡ እንዲያውም የበለጠ የፍቅር ጭብጨባቸው እንዲያምርበት፣ የልጆቻቸው ትዳር
የተባረከና የጸና እንዲሆን በበጎ አስተዋጽዖ ማዳማቅ ይችላል፡፡

ሁለታችሁም ማወቅ ያለባችሁ፣

የተጋባችሁት እናንተ ሁለታችሁ ናችሁ፡፡የተዋደዳችሁት እንናተው ሁለታችሁ ብቻ ናችሁ፡፡ከዚህ ውጭ ግን ያገናችሁ ሌላ ነገር ከሆነ እርሱን ከትዳራችሁ ውስጥ ካላስወጣችሁት አልፎ አልፎም ቢሆን ብቅ ማለቱና ትዳራችሁንና አንድነታችሁን መገዳድሩ አይቀርም፡፡ ለምሣሌ፦ ጥቅም/ሃብት/ ሁኔታዎች፣ ስዎች፣…ወዘተ…ከሆነ እውነተኛውንና ንጹህውን መፈላለጋችሁን ያደበዝዘዋል፡፡ የተዋደዳችሁትና የተፈላለጋችሁት አንቺና እርሱ ብቻ መሆናችሁ፣ ማለትም ማንንም ምንንም ያልጨመረ መፈላለግና መዋደችሁ ግልጽና የጠራ ነገር መሆን አለበት ማለቴ ነው፡፡

ምክርን መፈለግ፣

በግልጽ መነጋገርና መተማመን ላይ ካልተደረሰ ለጊዜው የተሻሻለ ቢመስልም ቆይቶ ተመሳሳይ ነገር መደገሙ አይቀርም፡፡ ሰለዚህ ይህንን ነገር መሠረት ለማስያዝ የበሰሉ የእግዚአብሔር ሰዎች /አገልጋዮች/ በተለይም የትዳርን ጉዳይ ሊያማክሩ የሚችሉ ፣ ሁለታችሁንም የሚያውቁ- የቅርብ አገልጋዮቻችሁ በዚህ ጉዳይ እንዲመክሩአችሁ ፈቀዱ፡፡በግልጽም ቢያነጋግሩአችሁ መልካም ነው፡፡ ትዳሩ ማንም፣ ምንም ጣልቃ የማይገባበት የሁለታችሁ ብቻ መሆኑ ግልጽ መሆን አለበት፡፡የልጆቻችሁ ጤናማ ዕድገት እንዳይበላሽ ከፈለጋችሁና ተወቃሽ ወላጆች ላለመሆን ከፈለጋችሁ፣ቤታችሁን ሁለታችሁ ምሩት፡፡ የሆነ ኮሽታ በተሰማ ቁጥር የማይደነብርና አንዳች ከውጭ የሚስነዘር ጥቃትም ሆነ ጥያቄ በመጣ ቁጥር የማይበረግግ ልብ ይሁንላችሁ፡፡ መረሳት የሌለበት የትዳር ጀማሪው ልዑል እግ/ር ስለሆነ የቅርብ ምሥክርና ሁሌ በጓዳችሁም የሚሆነውን ሁሉ ተመልካች መሆኑን ነው፡፡ ፍጹም ትዳር በምድር ላይ ላይኖር ይችላል፡፡ይብዛም ይነስም ሁሉም ቤት በየደረጃው ተጋዳሮቶች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ቢሆንም ግን አንዱ የሌላውን ድካም እየሽፈነ በመሸካከምና በመረዳዳት አብሮ መኖር ከትዳር ዓላማ አንዱ ነው፡፡ ይህንንም ልብ ብትይው ጥሩ ነው፡፡

መረሳት የሌለበት ጉዳይ፣

ጠላት ሳይጣን በምድር ላይ በብርቱ የሚጠላውና የሚቃወመው ተቋም ቢኖር እግ/ር የመሠረተውን ቤተስብ ነው፡፡ቢፈቀድለትና ቢሳካለት ማፈራረስና መበታተን ከሚፈለጋቸው አንዱና ዋነኛው ቤተስብን መሆኑን ለሰከንድ እንኳ መዘንጋት የለብንም፡፡ ዲያብሎስ የእግዚአብሔር ጠላት ስለሆነ እግዚአሔር የመሰረተውን በጎና መልካም ነገር ሁሉ ለማፈራረስ የቆረጠና የጨከነ የክፋት እቅድ አለው፡፡ነገር ግን ሁሉን ቻዩ አምላክ ይህንን የክፋትና የተንኮል ሥራውን ከንቱ አድርጎበታል፡፡የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስ የእግ/ር ልጅ መድኃኒታችን ጌታ ኢየሱስ ተገልጧልና ድል የሕዝቡ ነው፡፡ስለዚህ በማንም በኩል በር አግኝቶ በክፉ ፍላጻው እንዳይወጋን በራችንን መዝጋት ያለብን እኛው ነን፡፡የኛን ድርሻና ሃላፊነት ከተወጣን ጌታ ሁሌም ታማኝ ነው፡፡ ይህ ተለመደ አባባል ብቻ ሳይሆን በተግባር ያየነውና የታማኝነቱን ምህረት የተቀብልን ሁሉ እናውቃለን፡፡ስለዚህ አንቺም ውድ እህቴ አይዞሽ! ብቻ ከአምላክሽ ጋር ተስማሚ እንጂ አትስጊ! አይተውሽምና፡፡

የግል ምክሬ ፣

ውድ እህቴ !!! ብልህ ሁኚ ፣ ባልሽን በጥበብ ያዢው፣ ቤተሰቡንም ሳይጠላ አንቺም ሳትጠያቸው ባልሽን የራስሽ ጓደኛና አፍቃሪ ባል ልታደርጊው ትቺያለሽ፡፡ብልህ ሴት ቤቷን በጥበብ ትሠራለችና፡፡አስቢበት! ትቺያለሽ! ባልሽ በእጅሽ ነው፡፡ በሌላው ነገር ላይ invest
ያደረግሽውን ጉልበትም ሆነ ጥረት በባልሽ ላይ አድርጊው ባላሽ የራስሽ ይሆናል፡፡ ሳይቆጥብ በልግስና ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ላይኛይቱን፣ ገርና እሺ ባይቱን ጥበብ ሰጪው አምላክ በዚህች ጥበብ ይባርክሽ፣ሰላም ለአንቺና ለቤትሽ ይሁን፡አሜን፡፡
Aug 10, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
Aug 10, 2011 ታርሟል
በጌታ የተወደዳችሁ ወገኖቼ እስካሁን የሰጣችሁኝን ምላሾች ስከታተል ቆይቻለሁ፡፡ ጌታ አምላክ ለቅንነታችሁ መልካሙን ሁሉ ያድርግላችሁ፡፡ እኔም እንግዲህ ውስጤን ለመቀየርና ሁኔታዎችን እንደምክራችሁ ለማድረግ እጥራለሁ፡፡ ለዚህም ጌታ ይርዳኝ! አሜን!!
በጣም ለምንወድሽ አካላችን የዘላለም እህታችን።
አንቺ ከአሸናዎች በላይ ነሽ በሱ በወደደሽ በጌታ በርቺ
you are in my thought and prayer I want you to know
you decision will matter not only on earth but also in havens
so. ጌታ ያክበርሽ ይባርክሽ
you are loved by God and by all of us
you are not alone who so ever read this will be praying for you.
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2020 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...