ዋና ገጽ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   ትምህርቶች   የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች   የነጻ መዝሙሮች   ነጻ ዳውንሎድ   ያግኙን   ጥያቄ መጠያየቂያ 
website search (GO!)
 
ዋና ገጽ » ጥያቄ መጠያየቂያ
Email this page to a friend   Wednesday, 20 January 2021
ዋና ገጽ
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
የመጽሐፍ ቅዱስ ማውጫ
የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ
አዮታ ሶፍትዌር
ትምህርቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች
የነጻ መዝሙሮች
ነጻ ዳውንሎድ
ያግኙን Contact us
ጥያቄ መጠያየቂያ Q&A
የእገዛ ገጽ Help

“እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።“
(መዝሙረ ዳዊት 27:14)

rss

Today's verse

መኖር መሞት ሆኖብናል እራስሽን አጥፊ አጥፊ ይለኛል ምን ይሻለኛለ?

ጌታን ከተቀበልኩ 7 አመት ሆኖኛል የሚግረማቸሁ ነገር አሁን 22 አመቴ ነው ገና የ10 አመት ልጅ እያለሁ ነው እናትና አባቴ የሞቱት ከዛም የመጨረሻልጅ ስለነበርኩ 7 ታላላክ እህትና ወንድሞች አሉኝ እቤት ወስጥ ካሉት ጋር መኖር ጀመርኩ ነገር ግን በጣም ከፍተኛ በደልና እነግለት እየደረሰብኝ ማደግ አይቀርም አደኩኝ እናቴን በጠም እወዳት ስለነበር በከፋኝ ቁጥር እስወን እያነሳሁ አለቅስ ነበር በሀዋላ ጌታን ተቀበለኩ እናቴ በጌታ ተለወጣ ማዘኔን እረሳሁ ከዛ ጌታን መቀበሌን ቤተሰቦቼ ሲሰሙ ብዙ መከራ ደረሰበኝ አለፈውም ብቻዬን እነደሆን ከነሱ ጋር መኖር እንደማልችል ነገሩኝ እናም ሰካሁን ደረስ ብቻዬን ነው የምኖረው የሚገረማችሁ ክዛሬ አንድ አመት ከ8 ወር በፊት የነበረኝ መንፈሳዊ ህይዎት በጣም ደስ የሚል ነበር ነገር እግዚአብሄር በህይወቴ ለውጥ ያመጣል ብዬ ጠብቄው ነበር ነገር ግን ስቃዬ እየበዛ መኖር እያቃተኝ መጣ ጌታ ሆይ በያንስ እንክዋን ሃሳቤን የማካፍለው የኔ የምለው ሰው ስጠኝ እረዳት የሚሆነኝ የሚያዝንለኝ እያልኩኝ እለምነው ነበር ብቻ ምን አለፋችሁ ካቅሜ በላይ ፈተናዎች ደረሱብኝ ችግሬን እነከዋን የማዋየው የምነግረው ከክርስቶስ ሌላ ማንም ሰው አልነበረኝም እናም በጣም ሲመረኘ በቃኝ ጌታ ሆይ መረረኝ የሆነ ህየወቴ ላይ ለውጥ አድርገህ ካላሳየህኝ መንገዴን ቀይሬ ወደ ሀጥያት እገባለሁ ከሞትኩም ለሙት አልኩ ከዛም ለቅሶዬ ሲበዛ መንገዴን ቀየርኩና ባለም ያለ ሰው ገዋደኛ ያዝኩ በጣም ጥሩ ሰው ነው አንድ አመት ከ8 ወር እሰካሁን ድረስ ቆይተናል ከእርሱ ጋር ሆኜ አላም ቢሰማኝም የክርስቶስ ፍቅር ግን ከልቤ መውጣት አቀተው እኔና ልጁ ስነገናኝ በጌታ መሆኔን እያወቀ ነው የገባበት ወደሌላ መለወጥ እነደማልችል ነግሬው አምኖበት ነበር የገባበት በህዋላ ግን ፍቅራችን ሲጨምር አብረን ለመኖር በምናስብበት ሰሀት እኔ የሱን እምነት እነድቀበል ፍላጎቱ እንዳለውና ካለሆነ ግን አብረን መኖር እነደማነችል እነዴውመ ወስኜ ውሳኔዬን እነድነግረውና እነድንለያይ ነገረኝ እኔ ደሞ በክርስቶስ ጉዳይ መደራደር እነደማለችልና ጌታን መተው ለኔ መሞት እንደሆነ ነገርት ደጋግሞ የሀሳብ ለውጥ እነዲኖረኝ ለመነኝ እኔ ደሞ በፊትም የሰራሁት ስህተት መሆኑን ከነገርኩት በህዋላ እምነቴን ሳለቀይር አብረን እንኑር አለኩት አልተስማማንም ተለያየን በጣም እቀደዋለሁ እራሴ ዞሮአል ጌታን እወደዋለሁ ያለሱ መኖር መሞት ነው ምንም እነከዋን ልጁን ብወደው ከጌታ ማንም ለኔ አይበልጥም ስለዚህ በአሁኑ ሰኣት በጣም ከፍቶኛል ምክንያቱም ልጁን ስለምወደው ውስጤ ትክክል አይደለም መጽናናት አቅቶኛል መሮኛል መኖር አስጠላኝ መሞት እየፈለኩ ነው ምንም ነገር አላስደስት በሎኛል . ውሳኔዬ ትክክል እንደሆነ አውቃለሁ ግን ማልቀስ ሆነ ስራዬ እድሌን አማርርኩት መፈጠሬን ጠላሁት ውስጤ ተረብሾአል ምን ይሻለኛል አፅናኑኝ እባኻችሁ ጸልዩልኝ፡፡
Aug 10, 2011 መንፈሳዊ ስም-አልባ የተጠየቀ

3 መልሶች

0 ድምጾች
የኔ እህት ሕይወት ብዙ ውጣውረድ እና በፈተና የተሞላች ናት፡፡ ሁሉም ሰው የተለያየ ችግር ይገጥመዋል ዋናው ቁምነገር የተጋረጠብንን ችግር መወጣቱ ላይ ነው፡፡ አንቺ ያሰብሽው አማራጪ በጣም አስቸጋሪ እና እ/ርን የሚያሳዝን ነው ለሚያልፍ ቀን ብለሽ ሕይወትሽን ማጣት የለብሽም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ መከራና በገጠማችሁ ጊዜ እንደሙሉ ደስታ ቁጠሩት ይላል፡፡ አሁን የደረሰብሽ ችግር ነገ ሊገጥምሽ ካለው ክብር ጋር ሲነፃፀር በጣም ትንሽ ነው፡፡ ደግሞም ማን የሰራውን ነብስ ማን ያጠፋዋል? ፀልይ ጌታም ይሰማሻል፡፡ ጌታ ካንቺ ጋር ይሁን፡፡
Aug 10, 2011 እንያት ፀጋዬ (2,060 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
አይዞሽ እህቴ ሁሉም ያልፋልና ታገሺ። ስሜት ጊዜያዊ ነው ይለዋወጣልና ለጊዜው በሚሰማሽ ስሜት ተገፋፍተሽ የዘላለም ጸጸት ወደሚሆንና ልትለውጪው ወደማትችይው መውጫ ወደሌለው ስህተት ውስጥ እንዳትገቢ።

አየሽ በፊት የብቸኝነት ስሜትን መቋቋም አቅቶሽ የማይሆን ግንኙነት ጀመርሽ፤ ማለትም የብቸኝነት ስሜት ገፍቶሽ ማለት ነው። አሁን በዚያን ጊዜ ውሳኔሽ ትጸጸቺያለሽ። አሁን ደግሞ ከሚሰማሽ ስሜት መውጫ እግዚአብሔርን ታግሰሽ ከመጠበቅ ይልቅ የራስሽ የሆነ መፍትሄ ልታመጪ ታስቢያለሽ። ነገር ግን መጨረሻው የማትወጪበት የዘላለም ጸጸት ነውና አትቸኩዪ። የብቸኝነትን፣ የሃዘንን፣ የመዋረድን፣ የማጣትን፣ የህመምን፣ የበሽታን ወዘተ ስሜት አሸንፎ ማለፍ አንዱ በሕይወት የምንማረው ቁም ነገር ነውና፤ ትምህርት ቤት ውስጥ እንዳለሽ ቆጥረሽ በትዕስት ተማሪ።

ፍቅረኛን ማጣት እጅግ ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ። ሆኖም ያንንም ቢሆን ማሸነፍ ይቻላል። ብዙ ሚሊዮኖች ሰዎችም ያንን አሸንፈዋል። በእንዲህ ያሉ ፈተናዎች ማለፍ እኛን ያጠነክረናል ትዕግስትን እንድንማርና ውሳኔዎችንም በችኮላና በስሜት ብቻ ተገፋፍተን እንዳንወስን ያስተምረናል። በሕይወታችን ከስኬቶቻችን ይልቅ፤ በውድቀታችንና በሽንፈታችን የምንማረው ትምህርት ይበልጣል። ስለዚህ ውድቀት፣ መሳሳት፣ መጸጸትና ሽንፈት አንዱ የሕይወት ክፍል ነው። ከተማርንበት ደግሞ በምንም የማይገኝ መምህር ነውና በአንቺ ላይ ብቻ የደረሰ አድርገሽ አትመልከችው።

ደግሞስ ክርስቶስ የደም ላብን፣ ፍርሃትን፣ ግርፋትን፣ እርቃኑን መዋረድን፣ በሚስማር በመስቀል ላይ መቸንከርን ወዘተ ተሸክሞና ቆስሎ የሞተው እኮ አንቺንና እኔን እንዲሁም ደግሞ የወንጌሉን የምስራች ቃል ገና ያልሰሙትንና ወደ ሲኦል የሚነዱትን ለማዳን ነው። ታዲያ እኛ መስቀሉን እየተሸከምንና መከራን እየተቀበልን ብዙዎችን ነፍሳት በወንጌል ከሲኦል እንድናወጣ ተጠራን እንጂ፤ በወንድ ወይም በሴት ፍቅር ምክንያት ራሳችንን እንድናጠፋና ራሳችን ወደ ሲኦል እንድንሄድ አልተጠራንም።

በመጨረሻም አንድ ታሪክ ነግሬሽ ልጨርስ። አንድ ታላቅ ንጉሥ አንዱን ጥበበኛ የወርቅ አንጥረኛ (ሠሪ) ጠርቶ፤ እባክህን እዚህ ቀለበቴ ላይ ሳዝን የሚያጽናና እንዲሁም ደግሞ ስጠግብ የሚገስጽና የሚያስጠነቅቀኝ አንድ ቃል ጻፍልኝ ብሎ ይጠይቀዋል። የወርቅ አንጥረኛውም የንጉሡን ቀለበት ወስዶ "ሁሉም ያልፋል" የሚል ቃል ጻፈለት። ንጉሡም አንጥረኛው ለምን ይህንን ቃል እንደጻፈ ሲጠይቀው፤ ሃዘኑም፣ መከራውም፣ ለቅሶውም፣ ሰቆቃውም፣ ደስታውም፣ ጥጋቡም፣ ፈንጠዝያውም፣ ክብሩም ሁሉም ያልፋልና ብሎ መለሰለት ይባላል።

የወንድ ፍቅርን ማጣትም ያልፋል፣ ይረሳል! ጨለማ የሚመስለውም ስሜት ያልፋል! ትዕግስቱንና እድሜውን እግዚአብሔር ከሰጠን ሁሉም ሲያልፍ እናየዋለን።
Quote:
ኦሪት ዘፍጥረት
41፥51 ዮሴፍም የበኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፥ እንዲህ ሲል፦ እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት አስረሳኝ

ሕይወት ስኬትና ድል ብቻ ብትሆን ኖሮ፤ አንዳች የረባ ትምህርት ሳንማርባት ባለፈች ነበር።

ወደ ጌታሽ ጩኺ፣ እርሱም ከዚህ ሃዘን ብቻ ሳይሆን ከሌላም ሁሉ እንደሚያወጣሽ እስከ ሽበትና እስከ ሽምግልናም እንደሚሸከምሽ እመኚ! እግዚአብሔር ይጠብቅሽ!
Aug 10, 2011 በምሕረቱ (1,510 ነጥቦች) የተመለሰ
0 ድምጾች
ውድ እህቴ ሆይ! የገጠመሽ ጉዳይ ቀላል ባይሆንም እስቲ ለአንዳፍታ ጭክነሽ ያለሽበትን ሁኔታ ተወት አድርጊና በተከፈተ ልብ ስሚኝ! እግ/ር የልብሽን ጮኸትና የውስጥሽን ሰቆቃ ይስማልሽ፡፡ የምልሽ አንድ ነገር ብቻ ነው፣በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነሽ መቀበል ባትችይም ጌታ ስለአንቺ ያስባል፣ ይወድሻል፣ ምናልባትም በዚህ መንገድ ማለፍ የግድ ሊሆንም ይችላል፡፡ ስለሆነም ከክፉው ሃስብ ተጠበቂ ሃሳቡንም አትሳች፡፡ ምክኒያቱም፣ የጌታ ቃል እንደሚመክረን...

ሌባው ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ እንጂ ስለሌላ አይመጣም ፣እኔ ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ እንዲበዛላችሁም መጣሁ ፣ያለውን የጌታን ቃል አስቢ፡፡ ጌታ ሕይወት ሆኖልሽ እስከዛሬ መልካሙን የሕይወት መዓዛ ቀምሰሽል፣ጌታን ሳታውቂ የነበረሽን የኑሮ ዓይነት አትረሽውም፡፡ ሕይወት ይሽልሻልና የሕይወትን ጌታ ትተሽ ለእርድ እያዘጋጀሽ ያለውን የሌባውን ድምፅ አትታዘዥ፣ „ራስሽን አጥፊ አጥፊ እያለ በውሸት የሀዘኔታ ድምጽ የመጣው ቀጥሎ የማጥፊያውን መሳሪያ ያቀብልሻል፣ምክኒያቱም እርሱ ነፈሰ ገዳይ ስለሆነ ትጋቱ ሁሉ ለግድያና ሕይወትን ለማጥፋት ነው፡፡ የቀራኒዮው በግ ግን ስለአንቺ በመስቀል ላይ ሕይወቱን ሰጥቶ ደሙን አፍስሶ ከዘለዓለም ጥፋት ታድጎሻልና የፍቅር ውለታ የዋለልሽን የዘለዓለም ወድጅሽን አታሳዝኚው፣ የደሙ ፍሬ ነሽና ስለአንቺ የፈሰሰውን የወዳጅሽን ክቡር ደም ዋጋ አታሳንሽበት፡፡ውድ እህቴ ጌታ ከምን እንዳዳነሽ ረጋ ብለሽ ብታስቢው ሥጋ ለባሽ ሰው ከዳኝ፣ጓደኛዬ ተወኝ ብለሽ ሞትን አትመኚውም ነበር፡፡ውድ እህቴ ሆይ! ስሚኚ! እስቲ አንድ ጊዜ ስሚኝ!ቆም በይና አስቢ፡፡ ይህ ሰው እንደገና ተመልሶ ቢቀበልሽና ነገ ደግሞ አይኖሩ ኑሮ ቢያኖርሽ፣ወይም ጌት የምድር ዘመንህ በቃ ቢለው ፣ አሁንም ተስፋሽ እኮ ጌታ ብቻ ነው፡፡እርሱ ብቻ ነው የማይለውጥብሽ፣ፍቅሩ የማያረጅብሽ፣ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የወደደሽ ፣ ልጄ እንቺ የኔ ነሽ አልተውሽም አልጥልሽም፣ብሎ በቁልምጫ ስም የሚጠራሽ አምላክሽ ብቻ ነውና አትታለይ፡፡ ያዘነልሽ መስሎ ወደማትመለሽበት ጥልቅ ውስጥ ሊወረውርሽ የሚያባብልሽ እርሱ ሌባው ነውና ንቂበት፡፡ ልብ በይ! አንዴ የተተኮስ ጥይት በምንም ዓይነት መንገድ ወደኋላ መመለስ አይቻልም፡፡ ኢላማውን ቢመታም ባይመታም ከተተኮሰ ተተኮስ አበቃ! ጠላትሽ ያመጣልሽ የሞት መፍትሔ ዋጋው ውድ ነው፡፡ ሲኦል መንገዱ ሩቅ ነው፣ ቅርብ አይደለም፣ወደኋላ የመመለሻ መንገድ ጨርሶ የለውም፡፡

ዲያብሎስ ይህንን በውል ስለሚያውቅ መልካም አስመስሎ፣ከጊዜያዊ ትንሽ ችግር የመገላገያ መንገድ አስመስሎ እንደቀላልና ጥሩ አማራጭ የሞትን ግብዣ ለሰዎች ያቀርባልና አንቺ ግን አትስሚው፡፡ ስሚኝ ውድ የጌታ ልጅ! ስለ እምነትሽ ዋጋ የመክፈል እድል ገጥሞሻልና ልብሽ ይጽና ብድራትሽ ታላቅ ነው፡፡ጌታን ትተሽ ጓደኛሽ ያቀረብልሽን ምርጫ ብትቀብይ ለጥቂት ጊዜ ከጓደኛሽ ጋር ደስ ልልሽ ይችል ይሆናል፡፡ቀጥሎ ደግሞ ምን እንደሚሆን ማን ያውቃል?? ጥሩ ምርጫ መረጠሻልና አትፊሪ! ጌታን መምረጥ የምርጫ ሁሉ ቁንጮ ነውና ደስ ይበልሽ፡፡ እንዲያውም አንቺ አሸንፈሻልና ደግመሽ ደስ ይበለሽ፡፡አሁን የሚሰማሽ የተስፋ መቁረጥና የሀዘን ሰሜት ከጥቂት ጊዜ በኋላ ብትፈልጊም አታገኝአቸውም፡፡ ዞር ብለሽ ስታስቢው እንኳ ትንቂያቸዋለሽ፡፡ውድ እህቴ ሆይ! አንዴ ከተወረወሩበት በኋላ ተመልሶ መውጣት ወደማይቻልበት የጥፋት ሥፍራ ሊወረውርሽ የሚተጋውን የሌባውን ድምጽ አትስሚ፡፡አንቺ ከአሸናፊዎች ወገን ሆነሽ ሳለሽ የከሰርሽ አስመስሎ የሀዘን ደመናና የተስፋ መቁረጥ ጭጋግ በዙሪያሽ እንዲያንጃብብ የሚያደርገው ከተሰለፍሽበት የአሽናፊዎችና ከድል ነሺዎች ሠፈር ሊያወጣሽ እንደሆነ ለአንዳፍታ እንኳ አትዘንጊ! አንቺ የጌታ ልጅ ነሽና ፈተና በየፈርጁ ሊጋፈጥሽ ይችላል፡፡ሆኖም ከፈተናዎቻችን ውስጥ የመንወጣበትን የመውጫ መንገድ ጌታችን ለልጆቹ አለው፡፡

እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል፥ ስለዚህም እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት እንችላለን። (2ኛ ቆሮንቶስ 1፥4)

ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።(1ኛ ቆሮንቶስ 10፥13)

ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤ (ሮሜ 5፥3-4)

በመከራችን ረድኤትን ስጠን የሰውም ማዳን ከንቱ ነው። (መዝሙረ 60፥11 )

እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።(ዕብራውያን 4፥16)

የተወደድሽ እህታችን በመከራችን ሊያጽናና ሊረደን ወደሚችል ጌታ አብረንሽ እንጸልያለንና አይዞሽ ተስፋ አትቁርጭ፡፡ጌታ መልካም ነው፡፡ የሚራራ የሚምርም አምላክ ስለሆነ ይሰማናል፡፡ብቻ አሁን ባለሽበት ሁኔታ ወደጸጋው ዙፋን ፊት ለመቅረብ ሞክሪ፣አስቀድመሽ ግን ሰምተሽ ስላስተናገድሽው የሌባው ድምጽ ጌታን ምህረት ጠይቂ፡፡ በትህትና ወደነፍስሽ እረኛና ጠባቂ ተመለሺ የፍቅር እጆቹን ዘርግቶ ይቀበልሻል፡፡የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛልሽ፡፡
Aug 12, 2011 ስም-አልባ የተመለሰ
ላፅናናችሁኝ እና ለመከራችሁኝ እህትና ወንድሞቼ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ እሺ ምክራችሁን ተቀብያለሁ እራሴንም አላጠፋም ለሰይጣንም አልሸነፍም ፡፡ በእረግጥ ልቤ ተሰብሮአል ግን ጌታ ይጠግነግነኝ ልክ ናችሁ ለሚያለፍ ቀን ብዬ እራሴንና አምላኬን ማሳዘን አይገባኝም፡፡ ከመጀመሪያውም እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ ስገባ ነው እራሴን የገደልኩት ስለዚህ ልማርበት ስለሚገባገባኝ እማርበታለሁ ስለወደፊቱ እግዚአብሄር አዋቂ ነው፡፡ ከእነገዲህ እንደዚህ አይነት ስህተትን አልደግምም፡፡ አመሰግናለሁ ፀልዩልኝ መንገዴ እንዲስተካከል?
ያአገር ልጅ። ለኹሉም በርቺ። እግዜሩ ብርታቱንና ከፈተናሽ ማዕበል የምትወጪበትን ጥበቡን ይስጥሽ። ግን እስኪ ደግሞ አንቺ ራስሽ አስቢው ጌታ ክርስቶስን እወድደዋለሁ እያልሽ ግና ሞትን መመኘትሽ እንዴት ይኾናል?። ኹሌም ከርሱ ጎን የማትጠፋው፥የዘላለም እናቱ እመቤቴ ርሷ አለሁ ትበልሽ። ደግሞ ጨዋ ልጅ ያለናቱ ፈቃድ እንዳች ላይፈጽም ፡ ሰው የኾነው ጌታም ያለእመቤቴ እናትነት አንዳች ላያደርግ ግልጽ ነው። እና ግና እስኪ በርቺ። ኽሉም ያልፋል።
“እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።“
(መዝሙረ ዳዊት 33:12)

rss

Today's proverb

የኒውስ ሌተር ምዝገባ
የእርስዎ ስም ኢሜል አድራሻዎ ኢሜል አድራሻዎ (በድጋሚ)
»የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ   የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፈለጊያ
Copyright © 2004-2021 by iyesus.com
Terms of use | Contact us
...